ሐሰተኛ እና የተደጋገመ ደረሰኝ በታማኝነት ለሚሠሩ ንግዶች የቆየ ችግር ነው። የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ይህን ክፍተት ለመዝጋት የታሰበ ነው፦ እያንዳንዱ ሕጋዊ ደረሰኝ ለገዢው ከመድረሱ በፊት በገቢዎች ሚኒስቴር ሥርዓት ይመዘገባል።
ይህ የሚጠቅምዎት ግን ምን መመልከት እንዳለብዎት ካወቁ ነው። ይህ ጽሑፍ ደረሰኝ ለሚቀበል ሰው ነው፦ ለባለቤቱ፣ ለግዢ ሠራተኛው ወይም ለሂሳብ ባለሙያው።
ደረሰኝን ሕጋዊ የሚያደርገው ምንድን ነው?
በመመሪያ ቁጥር 1142/2018 መሠረት ፈቃድ ያለው ሥርዓት እያንዳንዱን ሽያጭ በዚያው ቅጽበት ወደ ሚኒስቴሩ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ይልካል። ሥርዓቱ አረጋግጦ የመመዝገቢያ ቁጥር እና ኪውአር ኮድ ይመልሳል። ደረሰኙ ሕጋዊ የሚሆነው እነዚህ ሲመለሱ ብቻ ነው። ለርዕሱ አዲስ ከሆኑ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምንድን ነው? ማንን ይመለከታል? የሚለውን ያንብቡ።
ደረሰኙ ላይ መመልከት ያለብዎት ሦስት ነገሮች
የመመዝገቢያ ቁጥር። በሚኒስቴሩ ሥርዓት የተሰጠ መለያ ቁጥር (IRN ወይም RRN)።
ኪውአር ኮድ። ሻጩ ራሱ ያዘጋጀው ሳይሆን በሚኒስቴሩ ሥርዓት በኩል የተሰጠ።
መሠረታዊ መረጃዎች በትክክል። የሻጩ ስም እና ቲን፣ እንደ ንግድ ድርጅት የሚገዙ ከሆነ የእርስዎ ቲን፣ ቀኑ፣ የዕቃዎቹ ዝርዝር፣ ቫቱ እና ጠቅላላ ድምሩ።
እንዴት ያረጋግጣሉ?
የስልክዎን ካሜራ ወይም የኪውአር ስካነር ከፍተው ኮዱን ስካን ያድርጉ።
ወደ ገቢዎች ሚኒስቴር የማረጋገጫ አገልግሎት የሚወስደውን ሊንክ ይክፈቱ።
ሚኒስቴሩ የሚያሳየውን በእጅዎ ካለው ደረሰኝ ጋር ያነጻጽሩ። ሻጩ፣ ቀኑ እና የገንዘቡ መጠን መገጣጠም አለባቸው።
ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ይወስዳል። ለትልልቅ ግዢዎች ልማድ ቢያደርጉት ይጠቅምዎታል።
ካልተረጋገጠስ?
ወዲያውኑ ማጭበርበር ነው ብለው አይደምድሙ፤ ስህተት ሊፈጠር ይችላል። ሆኖም እንዳለ ተቀብለው አያስቀምጡት። ሻጩ ደረሰኙን በትክክል እንዲቆርጥልዎት ይጠይቁ። ያልተመዘገበ ደረሰኝ እንደ ሕጋዊ የግብር ሰነድ ተቀባይነት ላያገኝ ስለሚችል፣ ለቫት ወይም ለወጪ ከመጠቀምዎ በፊት ከሂሳብ ባለሙያዎ ጋር ይነጋገሩ።
ደረሰኙ ስህተት ካለበትስ?
በመመሪያው መሠረት የተመዘገበ ደረሰኝ ተቀዶ እንደገና አይጻፍም። የዋጋ ማስተካከያ በታክስ ክሬዲት ኖት እና ዴቢት ኖት ይከናወናል፤ ደረሰኝ ለመሰረዝ ደግሞ በሥርዓቱ በኩል ጥያቄ ቀርቦ መጽደቅ አለበት። ሻጩ “በእጅ እናስተካክለው” ካለዎት ጥንቃቄ ያድርጉ።
ሻጭ ከሆኑ
ይህ ሁሉ ለእርስዎ ይጠቅማል። ደንበኞችዎ ደረሰኝዎን በሰከንዶች ማረጋገጥ ሲችሉ ይተማመኑብዎታል። ፈቃድ ባለው አገልግሎት ሰጪ ሲጠቀሙ የመመዝገቢያ ቁጥሩ እና ኪውአር ኮዱ በእያንዳንዱ ሽያጭ ላይ በራሱ ይጨመራል። አገልግሎት ሰጪ እየመረጡ ከሆነ የተፈቀደ አገልግሎት ሰጪ ለመምረጥ የሚረዱ 7 ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ።
የተመዘገበ ደረሰኝ ራስዎ ይመልከቱ
Ledger Technology PLC በመመሪያ ቁጥር 1142/2018 መሠረት የሽያጭ መመዝገቢያ SaaS አገልግሎት እንዲሰጥ በገቢዎች ሚኒስቴር ፈቃድ ያገኘ አቅራቢ ነው። በነፃ ማሳያ ላይ ደረሰኝ እንዴት እንደሚቆረጥ እና እንደሚረጋገጥ እናሳይዎታለን።
በቴሌግራም ነፃ ማሳያ ይያዙ፦ t.me/ledgersalesbot
ይህ ጽሑፍ አጠቃላይ መረጃ እንጂ የግብር ምክር አይደለም። ለእርስዎ ሁኔታ የሂሳብ ባለሙያዎን ወይም የገቢዎች ሚኒስቴርን ያማክሩ።



